Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




አሞጽ 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከአንበሳ ፊት ሲሸሽ ድብ እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይህ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ፣ ድብ እንደሚያጋጥመው፣ ወደ ቤቱም ገብቶ፣ እጁን በግድግዳው ላይ ሲያሳርፍ፣ እባብ እንደሚነድፈው ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።

See the chapter Copy




አሞጽ 5:19
12 Cross References  

አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።


በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ።


ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።


ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ወደ ዋሻው አፍ ታላላቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ፥ እንዲጠብቋቸው ሰዎችን በዚያ አኑሩ፤


የድኾችን መብት ለሚገፉ፤ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፤ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፤ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!


በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements