አሞጽ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደ ሆነ፣ በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና። ጻድቁን ትጨቍናላችሁ፤ ጕቦም ትቀበላላችሁ፤ በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በደላችሁ ምን ያኽል እንደ በዛና ኃጢአታችሁም ምን ያኽል ከባድ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ደጋግ ሰዎችን ታስጨንቃላችሁ፤ ጉቦ እየተቀበላችሁ በየፍርድ አደባባዩ የምስኪኖችን ፍትሕ ታጣምማላችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኀጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ ዐውቃለሁና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና። See the chapter |