አሞጽ 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 “እኔ በከተማችሁ ሁሉ ራብን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት አመጣባችኋለሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 “በየከተማው ጥርሳችሁን አጠራለሁ፤ በየመንደሩም የምትበሉትን አሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 “በአፋችሁ የምትቀምሱት እህል አሳጥቼ በከተሞቻችሁ ሁሉ ችጋር ለቅቄባችኋለሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 “በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥረስን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣትን ሰጠኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ይላል እግዚአብሔር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥራት፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት ሰጠኋችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር። See the chapter |