Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




አሞጽ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እያንዳንዳችሁ እፊታችሁ ባለ በተነደለ ስፍራ በኩል ትወጣላችሁ፤ ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፥” ይላል ጌታ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያ ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እያንዳንዳችሁ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው መሹለኪያ ቀዳዳ ተጐትታችሁ በመውጣት ወደ ሃርሞን ትጣላላችሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁን ያወ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ትተ​ያ​ያ​ላ​ችሁ፤ በሬ​ማ​ንም ተራራ ትጣ​ላ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እያንዳንዳችሁ በየፊታችሁ በተነደለ ስፍራ ትወጣላችሁ፥ በሬማንም ትጣላላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

See the chapter Copy




አሞጽ 4:3
12 Cross References  

እያዩህም ግንቡን ቦርቡረው፥ በእርሱም አውጣው።


በመካከላቸውም ያለው ልዑል በትከሻው ላይ ተሸክሞ በጨለማ ይወጣል፥ በዚያም ሊወጡ ግንቡን ይቦረቡራሉ፥ በዓይኑም ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።


በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉ።


በዚያን ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፤ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።


የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።


ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።


ገለዓድ በዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፥ ዳንም ለምን በመርከብ ውስጥ ቀረ? አሴርም በባሕሩ ዳር ተቀመጠ፥ በወንዞቹም ዳርቻ ዐረፈ።


የከተማይቱም ቅጥር ተጣሰ፥ ወታደሮችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥሮች መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ዓረባም በሚወስደው መንገድ ሄዱ።


ስለዚህ በመጀመሪያ ተማርከው ከሚፈልሱት ይሆናሉ፥ እንደ ፈቃዳቸው ከሚሆኑ መካከል ፈንጠዝያ ይርቃል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements