Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 4:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እነርሱም እንደምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንደ ገና ከዛቱባቸው በኋላም ለቀቋቸው፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ስለ ነበር ሊቀጧቸው አልቻሉም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሕዝብ አለቆችና የሸንጎው አባሎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን የሚያስቀጣ ምንም ምክንያት ባለማግኘታቸው፥ ሕዝቡንም ስለ ፈሩ እንደገና አስጠንቅቀው ለቀቁአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግን ስለ ነበር ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እነርሱም እንደ ምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደ ገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 4:21
18 Cross References  

በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፤ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።


የካህናት አለቆችና ጻፎች እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።


የካህናት አለቆችና ጻፎችም ይህን ምሳሌ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረ አውቀው በዚያች ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ።


‘ከሰዎች’ ብንል ግን ሕዝቡ ሁሉ በድንጋይ ይወግሩናል፤ ምክንያቱም ዮሐንስ ነቢይ እንደ ነበረ ሁሉም ያምኑ ነበርና” አሉ።


ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡ እንደ ነቢይ ያዩት ስለ ነበር ፈሩ።


ሕዝቡም ይህንን አይተው ፈሩ፤ እንዲህ ያለውንም ሥልጣን ለሰው በመስጠቱ እግዚአብሔርን አከበሩ።


ሰሙትም፤ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፤ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።


ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ።


ይህንንም ሲናገር የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ በእርሱም በተደረጉት ድንቅ ነገሮች ሁሉ ሕዝቡ በሙሉ ደስ አለው።


ሁሉም ተገረሙ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ በፍርሃትም ተሞልተው፦ “ዛሬስ አስደናቂ ነገሮችን አየን፤” አሉ።


ነገር ግን “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይነሣ በበዓል ቀን አይሁን” አሉ።


ሕዝቡም ዲዳዎች ሲናገሩ፥ ሽባዎች ሲፈወሱ፥ አንካሶች ሲራመዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።


ጋኔኑ ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም ተደንቀው “እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ከቶ ታይቶ አይታወቅም” አሉ።


ይህ የመፈወስ ምልክት የተደረገለት ሰው ከአርባ ዓመት ይበልጠው ነበርና።


ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements