Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 27:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ያድነው ዘንድ አስቦ ምክራቸውን ከለከለ፤ ዋና የሚያውቁትም ከመርከብ ራሳቸውን እየወረወሩ አስቀድመው ወደ ምድር ይወጡ ዘንድ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ እንዲተርፍ ስለ ፈለገ፣ ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ ከለከላቸው፤ መዋኘት የሚችሉ ከመርከብ እየዘለሉ አስቀድመው ከባሕሩ ወደ ምድር እንዲወጡ፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ስለ ፈለገ አሳባቸውን አልተቀበለም፤ ይልቁንም መዋኘት የሚችሉ አስቀድመው ከመርከቡ ወደ ባሕር እየዘለሉ ወደ ምድር እንዲወጡ አዘዘ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 የመቶ አለ​ቃው ግን ጳው​ሎ​ስን ሊያ​ድ​ነው ወድ​ዶ​አ​ልና ምክ​ራ​ቸ​ውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም ዋኝ​ተው ወደ ምድር እን​ዲ​ወጡ አዘ​ዛ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ያድነው ዘንድ አስቦ ምክራቸውን ከለከለ፤ ዋና የሚያውቁትም ከመርከብ ራሳቸውን እየወረወሩ አስቀድመው ወደ ምድር ይወጡ ዘንድ፥

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 27:43
8 Cross References  

በነገውም ወደ ሲዶና ስንደርስ ዩልዮስ ለጳውሎስ ቸርነት አድርጎ እርዳታቸውን ይቀበል ዘንድ ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድ ፈቀደለት።


የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።


ሦስት ጊዜ በበትር ተመትቻለሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬለሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰባብሯል፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖሬለሁ።


የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ ከተናገረው ይልቅ የመርከብ መሪውንና የመርከቡን ባለቤት ያምን ነበር።


ጳውሎስንም ወደ አገረ ገዢው ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲያደርሱት የሚያስቀምጡበትን ከብት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው።


ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።


ጳውሎስ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮች “እነዚህ በመርከቡ ካልቆዩ እናንተ ትድኑ ዘንድ አትችሉም፤” አላቸው።


ወታደሮቹም ከእስረኞች አንድ ስንኳ ዋኝቶ እንዳያመልጥ ይገድሉአቸው ዘንድ ተማከሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements