ሐዋርያት ሥራ 27:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተ ኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፤ ቀንም እንዲሆን ተመኙ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ከቋጥኞቹም ጋራ እንዳንላተም በመፍራት፣ አራት መልሕቆች ከመርከቡ በስተኋላ ጣሉ፤ ምነው በነጋ እያሉም ይለምኑ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 መርከባችን በባሕሩ ዳር ካሉ ድንጋዮች እንዳይጋጭ ፈርተው ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቆችን ወደ ባሕሩ አወረዱ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ አልፎ ቀን እንዲመጣላቸው ይጸልዩ ጀመር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ድንጋያማ በሆነ ቦታም እንዳይወድቁ ፈሩ፤ ስለዚህም ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቅ በባሕሩ ላይ ጣሉ፤ ፈጥኖ እንዲነጋም ጸለዩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፥ ቀንም እንዲሆን ተመኙ። See the chapter |