ሐዋርያት ሥራ 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ወደዚህም ወደ ተስፋ ቃል ዐሥራ ሁለቱ ወገኖቻችን ሌሊትና ቀን በትጋት እያመለኩ ይደርሱ ዘንድ አለኝታ አላቸው፤ ስለዚህም አለኝታ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! ከአይሁድ እከሰሳለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ከልብ እያገለገሉ፣ ሲፈጸም ለማየት የሚተጉለትም ተስፋ ይኸው ነው። ንጉሥ ሆይ፤ አይሁድም የሚከስሱኝ ስለዚሁ ተስፋ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ወደዚህ ተስፋ ለመድረስ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን እግዚአብሔርን ሌት ተቀን እያመለኩ ይጠባበቁ ነበር፤ ንጉሥ ሆይ! እኔም በአይሁድ የተከሰስኩበት በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን በመዓልትም በሌሊትም እርሱን እያገለገሉ ወደ እርስዋ ይደርሱ ዘንድ ተስፋ ያደርጋሉ፤ አይሁድም የሚከስሱኝ ስለዚህ ተስፋ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ወደዚህም ወደ ተስፋ ቃል አሥራ ሁለቱ ወገኖቻችን ሌሊትና ቀን በትጋት እያመለኩ ይደርሱ ዘንድ አለኝታ አላቸው፤ ስለዚህም አለኝታ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ ከአይሁድ እከሰሳለሁ። See the chapter |