ሐዋርያት ሥራ 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አሁንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ስለ ተስፋ ቃል አለኝታ ልፋረድ ቆሜአለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አሁንም ተከስሼ እዚህ የቀረብሁበት ምክንያት፣ እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ቃል የገባውን ነገር ተስፋ በማድረጌ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አሁን ግን ለፍርድ እዚህ የቆምኩት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ስለ ሰጠው የቃል ኪዳን ተስፋ ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አሁንም ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን የተሰጠውን ተስፋ በመታመን ከፍርድ በታች ቆሜአለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አሁንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ስለ ተስፋ ቃል አለኝታ ልፋረድ ቆሜአለሁ። See the chapter |