Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 25:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በቀረበም ጊዜ ከኢየሩሳሌም የወረዱት አይሁድ ከበውት ቆሙ፤ ይረቱበትም ዘንድ የማይችሉትን ብዙና ከባድ ክስ አነሱበት፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጳውሎስ በቀረበ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ ከበቡት፤ በማስረጃ ያልተደገፉ ብዙ ከባድ ክሶችም አቀረቡበት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ጳውሎስ በቀረበ ጊዜ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ ከበውት ቆሙና ማስረጃ ሊያገኙለት የማይችሉትን ብዙ ከባድ ክስ አቀረቡበት፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የወ​ረዱ አይ​ሁድ ከብ​በ​ውት ቆሙ፤ ሊረቱ በማ​ይ​ች​ሉ​በ​ትም ብዙና ከባድ ክስ ከሰ​ሱት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በቀረበም ጊዜ ከኢየሩሳሌም የወረዱት አይሁድ ከበውት ቆሙ፥ ይረቱበትም ዘንድ የማይችሉትን ብዙና ከባድ ክስ አነሱበት፤

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 25:7
16 Cross References  

አሁንም ስለሚከሱኝ ያስረዱህ ዘንድ አይችሉም።


ፊስጦስም አለ “አግሪጳ ንጉሥ ሆይ! እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ።


የካህናት አለቆችና ጻፎችም በብርቱ እየከሰሱት ቆመው ነበር።


“ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር።


የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።


የሐሰት ምስክሮች ተነሡብኝ፥ የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ።


በአባቶችህ ታሪክ መጽሐፍ ምርመራ ይደረግ በዚያም በታሪክ መጽሐፍ ይህች ከተማ ዓመፀኛ እንደ ሆነች፥ ነገሥታትንና አውራጃዎችንም እንደ ጐዳች፥ ከጥንቱም ሽፍትነት በእርሷ እንደ ተጀመረ ታገኛለህ፥ ታውቃለህም፤ ስለዚህም ይህች ከተማ ፈርሳ ነበር።


በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና እንዲህ አሉት፦


ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements