ሐዋርያት ሥራ 25:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ፊስጦስም አለ “አግሪጳ ንጉሥ ሆይ! እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 በዚህ ጊዜ ፊስጦስ እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፤ እንዲሁም እዚህ ዐብራችሁን ያላችሁ ሁሉ፤ ይህን ሰው ታዩታላችሁ? በኢየሩሳሌምና እዚህ በቂሳርያም የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ ይህ ሰው ከእንግዲህ በሕይወት መኖር አይገባውም በማለት እየጮኹ ለመኑ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 እንዲህም አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ! አይሁድ ‘ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት መኖር አይገባውም’ በማለት እየጮኹ በኢየሩሳሌምም፥ በዚህም እንዲፈረድበት የጠየቁኝ ይህ የምታዩት ሰው ነው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ፊስጦስም እንዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ወንድሞቻችን ሁላችሁ፥ ስሙ፤ አይሁድ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው በኢየሩሳሌምም ሆነ በዚህ እየጮሁ የለመኑኝ ይህ የምታዩት ሰው እነሆ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ፊስጦስም አለ፦ “አግሪጳ ንጉሥ ሆይ እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ። See the chapter |