ሐዋርያት ሥራ 23:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ሰዱቃውያን “ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም፤” የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ሰዱቃውያን የሙታን ትንሣኤ የለም፤ መላእክትም መናፍስትም የሉም የሚሉ ሲሆኑ፣ ፈሪሳውያን ግን በእነዚህ ሁሉ መኖር የሚያምኑ ነበሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ሰዱቃውያን “ትንሣኤ የለም፤ መላእክትም የሉም፤ መንፈስም የለም” ሲሉ ፈሪሳውያን ግን “እነዚህ ሁሉ አሉ” ብለው ያምናሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ሰዱቃውያን፥ “ሙታን አይነሡም፤ መልአክም የለም፤ መንፈስም የለም” ይላሉና፤ ፈሪሳውያን ግን ይህ ሁሉ እንዳለ ያምናሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሰዱቃውያን፦ ትንሣኤም መልአክም መንፈስም የለም የሚሉ ናቸውና፤ ፈሪሳውያን ግን ሁለቱን ያምናሉ። See the chapter |