ሐዋርያት ሥራ 23:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 በዚህም ሰው አይሁድ ሤራ እንደሚያደርጉበት ባመለከቱኝ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ አንተ ላኩት፤ ከሳሾቹንም ደግሞ በፊትህ እንዳይከሱት ዘንድ አዘዝኋቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 አይሁድ ግን በዚህ ሰው ላይ ማሤራቸውን በተረዳሁ ጊዜ፣ ወዲያው ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹም ከርሱ ጋራ ያላቸውን ክርክር ለአንተ እንዲያቀርቡ አዘዝኋቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ይህን ሰው ለመግደል ሤራ እንደ ተደረገ በሰማሁ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹም በእርሱ ላይ ያላቸውን ክስ በአንተ ፊት እንዲያቀርቡ ነግሬአቸዋለሁ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 አይሁድም በዚህ ሰው ላይ በመሸመቅ የሚያደርጉትን በዐወቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹንም ወደ አንተ እንዲመጡና በፊትህ እንዲፋረዱት አዝዣቸዋለሁ፤ ደኅና ሁን።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 በዚህም ሰው አይሁድ ሴራ እንዲያደርጉበት ባመለከቱኝ ጊዜ ያን ጊዜውን ወደ አንተ ሰደድሁት፥ ከሳሾቹንም ደግሞ በፊትህ ይከሱት ዘንድ አዘዝኋቸው። ደኅና ሁን። See the chapter |