ሐዋርያት ሥራ 23:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው፤ የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፤” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ስለዚህ ዕሺ አትበላቸው፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከአርባ በላይ የሚሆኑት ሊገድሉት አድፍጠው እየጠበቁት ነው፤ ደግሞም እስኪገድሉት ድረስ እህል ውሃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን መልስ እየተጠባበቁ ነው።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ እርሱን ሳንገድል እህል አንበላም፤ ውሃም አንጠጣም በማለት የተማማሉ ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች እርሱን ለመግደል አድፍጠዋል፤ አሁን እነርሱ የሚጠብቁት የአንተን መልስ ብቻ ነው።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 አንተ ግን እሽ አትበላቸው፤ ሊገድሉት ሽምቀዋልና፤ እስኪገድሉትም ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ እንዲህ የተማማሉ ሰዎች ከአርባ ይበዛሉ፤ አሁንም እስክትልክላቸው ይጠብቃሉ እንጂ እነርሱ ቈርጠዋል።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ አለው። See the chapter |