ሐዋርያት ሥራ 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እነርሱም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎቹ መጥተው “ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ ምንም እንዳንቀምስ ተረጋግመን ተማምለናል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እነርሱም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎች ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ጳውሎስን ሳንገድል እህል ላለመቅመስ ጽኑ መሐላ አድርገናል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እነርሱ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎች ሄደው እንዲህ ሲሉ ነገሩአቸው፤ “ጳውሎስን ሳንገድል እህል እንዳንቀምስ በጥብቅ ተማምለናል፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እነርሱም ወደ ሊቃነ ካህናትና ወደ መምህራን ሄደው እንዲህ አሉአቸው፥ “ጳውሎስን እስክንገድለው ድረስ እነሆ፥ እንዳንበላና እንዳንጠጣ ፈጽመን ተማምለናል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እነርሱም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎቹ መጥተው፦ ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ ምንም እንዳንቀምስ ተረጋግመን ተማምለናል። See the chapter |