Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በአሕዛብ መካከል የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉና ልጆቻቸውን እንዳይገርዙ፣ በቈየው ልማዳችን መሠረት እንዳይኖሩ እንደምታስተምር ስለ አንተ ተነግሯቸዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አንተ በአሕዛብ መካከል የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ ‘ልጆቻችሁን አትግረዙ ወይም ሥርዓቶችን አትፈጽሙ’ እያልክ በማስተማር የሙሴን ሕግ እንዲሽሩ ታደርጋለህ እየተባለ የሚወራውን ሰምተዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ነገር ግን የማ​ይ​ሆ​ነ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ የሙ​ሴ​ንም ሕግ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ዋ​ቸው፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያሉ ያመኑ አይ​ሁ​ድ​ንም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ገ​ርዙ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ እን​ዳ​ይ​ፈ​ጽሙ እን​ደ​ም​ት​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸው ስለ አንተ ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ በሥርዓትም እንዳይሄዱ ብለህ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁድ ሁሉ ሙሴን ይክዱ ዘንድ እንድታስተምር ስለ አንተ ነግረዋቸዋል።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 21:21
12 Cross References  

ከሦስት ቀንም በኋላ ጳውሎስ የአይሁድን ታላላቆች ወደ እርሱ ጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው “ወንድሞች ሆይ! እኔ ሕዝቡን ወይም የአባቶችን ሥርዓት የሚቃወም አንዳች ሳላደርግ፥ ከኢየሩሳሌም እንደ ታሰርሁ በሮማውያን እጅ አሳልፈው ሰጡኝ።


ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፤ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።


እንግዲህ ምን ይሁን? የአንተን መምጣት ይሰማሉና ብዙዎች የግድ ሳይሰበሰቡ አይቀሩም።


ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements