Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 19:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ዛሬ ስለተደረገው ‘ሁከት ነው፤’ ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፤ ምክንያት የለምና።” ይህንም ብሎ ጉባኤውን ፈታው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 አለዚያ ዛሬ ስለ ሆነው ነገር፣ በሁከት አነሣሽነት እንዳንከሰስ ያሠጋናል፤ አጥጋቢ ምክንያት ስለሌለንም፣ ስለ ሁከቱ ብንጠየቅበት መልስ መስጠት አንችልም።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 አለበለዚያ ዛሬ በተደረገው ነገር ‘ሁከት አስነሥተዋል’ ተብለን እንዳንከሰስ ያስፈራል፤ ‘ይህ ብጥብጥ በምን ምክንያት ተነሣ’ ተብለን ብንጠየቅ የምንሰጠው መልስ የለንም”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ዛሬም በደል ሳይ​ኖር በአ​መ​ጣ​ች​ሁ​ብን ክር​ክር እኛ እን​ቸ​ገ​ራ​ለ​ንና ስለ​ዚህ ክር​ክር የም​ን​ወ​ቃ​ቀ​ሰው ነገር የለም፥” ይህ​ንም ብሎ ሸን​ጎ​ውን ፈታ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ዛሬ ስለ ተደረገው፦ ሁከት ነው ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፥ ምክንያት የለምና።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 19:40
10 Cross References  

አንተ ከዚህ ዘመን አስቀድሞ ከነፍሰ ገዳዮቹ አራቱን ሺህ ሰዎች አሸፍተህ ወደ ምድረ በዳ ያወጣህ የግብጽ ሰው አይደለህምን?” አለ።


ሊገድሉትም ሲፈልጉ “ኢየሩሳሌም ፈጽማ ታወከች፤” የሚል ወሬ ወደ ጭፍራው ሻለቃ ወጣ፤


ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፤ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ።


ነገር ግን “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይነሣ በበዓል ቀን አይሁን” አሉ።


አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፥ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምፅ በሰማ ጊዜ፦ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምፅ ምንድነው?” አለ።


እጅግ የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ብዙዎች በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ክስተቶች በጽሑፍ ለማዘጋጀት እንደሞከሩት ሁሉ፥


ስለ ሌላ ነገር እንደሆነ ግን አንዳች ብትፈልጉ፥ በተደነገገው ጉባኤ ይፈታል።


ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፤” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements