ሐዋርያት ሥራ 19:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለምን እንደተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ጉባኤውም ተበጣብጦ፣ አንዱ አንድ ነገር ሲናገር ሌላውም ሌላ እየተናገረ ይጯጯኽ ነበር፤ አብዛኛውም ሰው ለምን እዚያ እንደ ተሰበሰበ እንኳ አያውቅም ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 በሕዝቡ መካከል ታላቅ ሁከት ስለ ነበር አብዛኞቹ ለምን እንደ ተሰበሰቡ እንኳ አያውቁም ነበር፤ በዚህ ምክንያት አንዱ አንድ ነገር እያለ ሲጮኽ ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር እያለ ይጮኽ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 በዚያም በጨዋታው ቦታ የነበሩ ሰዎች እየጮኹ ቈዩ፤ በሌላም ቋንቋ የሚጮሁ ነበሩ፤ በጉባኤው ታላቅ ድብልቅልቅ ሆኖ ነበርና፤ ከእነርሱ የሚበዙት ግን በምን ምክንያት እንደ ተሰበሰቡ አያውቁም ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለ ምን እንደተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና። See the chapter |