Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 17:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 አንዳንድ ሰዎች ግን ጳውሎስ ባለው በመስማማት ተከተሉት፤ አመኑም፤ ከእነዚህም ዲዮናስዮስ የተባለው የአርዮስፋጎስ ፍርድ ቤት አባል፣ ደማሪስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ሰዎች ነበሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 አንዳንድ ሰዎች ግን ከእርሱ ጋር ተባበሩና አመኑ፤ ካመኑትም ሰዎች መካከል የአርዮስፋጎስ ጉባኤ አባል የሆኑት ዲዮናስዮስ የተባለ ሰውና ደማሪስ የተባለች አንዲት ሴት፥ ሌሎችም ይገኙባቸዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 አም​ነው የተ​ከ​ተ​ሉት ሰዎ​ችም ነበሩ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ ከአ​ር​ዮ​ስ​ፋ​ጎስ ባለ​ሥ​ል​ጣ​ኖች ወገን የሚ​ሆን ዲዮ​ና​ስ​ዮስ ነበር፤ ደማ​ሪስ የም​ት​ባል ሴትም ነበ​ረች፤ ሌሎ​ችም አብ​ረ​ዋ​ቸው ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 17:34
11 Cross References  

ይዘውም “ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን፤” ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ።


አሕዛብም ሰምተው ደስ አላቸው፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አከበሩ፤ ለዘለዓለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ፤


ቅዱሳን ሁሉ ይልቁንም ከቄሣር ቤት የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።


ጳውሎስም በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ “የአቴና ሰዎች ሆይ! እናንተ በሁሉ ነገር አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ።


ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።’”


እንዲሁም ጳውሎስ ከመካከላቸው ወጣ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements