Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 12:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይህን ከተረዳ በኋላም፣ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው በአንድነት ወደሚጸልዩበት፣ ማርቆስ ወደተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህን ካረጋገጠ በኋላ ብዙ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ወደሚጸልዩበት ወደ ማርያም ቤት ሄደ፤ ይህችም ማርያም ማርቆስ የተባለው የዮሐንስ እናት ነበረች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 12:12
14 Cross References  

ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።


አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።


በስልማናም በነበሩ ጊዜ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፤ አገልጋይም ዮሐንስ ነበራቸው።


በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።


እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።


ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስን ከአንተ ጋር ይዘኸው ና፥ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና።


“ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት፤” የሚል ትእዛዝ የተቀበላችሁለት የበርናባስ የወንድሙ ልጅ ማርቆስ እንዳረገው እንዲሁ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።


ጳውሎስም ከጓደኞቹ ጋር ከጳፉ ተነሥቶ የጵንፍልያ ወደምትሆን ወደ ጴርጌን መጣ፤ ዮሐንስም ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።


ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።


ተፈትተውም ወደ ወገኖቻቸው መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሉአቸውን ሁሉ ነገሩአቸው።


ከእናንተ ጋር የተመረጠችው፥ በባቢሎን ያለችው ቤተ ክርስቲያን፥ ልጄ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements