Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሐዋርያት ሥራ 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ይህም ሰው በዐመፅ ዋጋ መሬት ገዛ፤ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይህ ሰው ስለ ክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በዚያም በግንባሩ ተደፍቶ ሰውነቱ እመካከሉ ላይ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ነገር ግን ይህ ሰው በክፉ ሥራው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ተዘረገፈ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከዚ​ህም በኋላ ይህ ሰው በዐ​መፅ ዋጋዉ መሬት ገዛ፤ በም​ድር ላይም በግ​ን​ባሩ ወደ​ቀና ከመ​ካ​ከሉ ተሰ​ነ​ጠቀ፤ አን​ጀ​ቱም ሁሉ ተዘ​ረ​ገፈ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤

See the chapter Copy




ሐዋርያት ሥራ 1:18
12 Cross References  

ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።


መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ፥ በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን።


የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም ለምዋርቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃላት ነገሩት።


ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው፥ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱ ደግሞ አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ወደ ሌላ አገር ሄደ።


ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የምትነግረኝንም ሁሉ አደርግልሃለሁና፥ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።’ ”


ጌታም፦ ሊከፍሉኝ የተስማሙበት ጥሩ ዋጋ በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በጌታ ቤት ባለው ግምጃ ክፍል ውስጥ አኖርኩት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements