Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ጢሞቴዎስ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ ብዙ ክፉ ነገሮችን አድርጎብኛል፤ ጌታ እንደ ሥራው ብድራቱን ይከፍለዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አንጥረኛው እስክንድሮስ ብዙ ጕዳት አድርሶብኛል፤ ጌታ ግን የእጁን ይሰጠዋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።

See the chapter Copy




2 ጢሞቴዎስ 4:14
18 Cross References  

ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ከእነዚህ መካከል ናቸው፤ እነርሱም እንዳይሳደቡ ለማስተማር ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁ።


በእርግጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ ነውና፥ መከራን የሚያደርሱባችሁን በመከራ ብድራታቸውን ይከፍላል።


እንደ ሥራቸው እንደ አካሄዳቸውም ክፋት ስጣቸው፥ እንደ እጃቸውም ሥራ ስጣቸው፥ ፍዳቸውን ወደ ራሳቸው መልስ።


አባቴ ሆይ፤ የልብስህ ቁራጭ ይኸው በእጄ ላይ ተመልከተው! የልብስህን ጫፍ ቆረጥሁ እንጂ አንተን አልገደልኩህም። አሁንም ክፋት ወይም ዐመፅ አለመፈጸሜን ዕወቅልኝ፤ ተረዳልኝም፤ እኔ ክፉ አልሠራሁብህም፤ አንተ ግን ሕይወቴን ለማጥፋት እያሳደድኸኝ ነው።


እርሷ በሰጠችው መጠን መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤


“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።


አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስታውሰኝ ጐብኘኝም፥ የሚያሳድዱኝንም ተበቀልልኝ፤ ቁጣህንም ከማዘግየትህ የተነሣ እንዳታጠፋኝ፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።


እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፥ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥


ምንም እንኳ ዛሬ የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም፥ እኔ ደካማ ሰው ነኝ፤ እነዚህ የጽሩያ ልጆች እጅግ በርትተውብኛል። ጌታ ለክፉ አድራጊ የእጁን ይስጠው።”


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።


ማንም ወንድሙ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ እግዚአብሔርም ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ። ስለዚህ ይለምን አልልም።


እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል፤


አንተም ደግሞ ከእርሱ ነቅተህ ራስህን ጠብቅ፤ የምንናገረውን እጅግ ተቃውሞአልና።


ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements