2 ጢሞቴዎስ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አሁን ግን በወንጌል አማካይነት ሞትን በሻረው፥ ሕይወትንና ያለመበስበስን ወደ ብርሃን ባመጣው በአዳኛችን በክርስቶስ ኢየሱስ መገለጥ በኩል ተገለጠ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አሁን ግን ሞትን ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሕይወትንና ኢመዋቲነትን ወደ ብርሃን ባወጣው በመድኀኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ መምጣት ተገልጧል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ይህም ጸጋ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣቱ አሁን ተገለጠ። እርሱ የሞትን ኀይል ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሞት የሌለበትን ዘለዓለማዊ ሕይወት ገለጠልን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10-11 አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና፤ እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10-11 አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል። See the chapter |