Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 7:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በፊትህ ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር፥ አሁንም የአገልጋይህን ቤት እባክህ ባርክ። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አንተው ራስህ ተናግረሃል፤ በበረከትህም የአገልጋይህ ቤት ለዘለዓለም ይባረክ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በፊትህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር፣ አሁንም የባሪያህን ቤት እባክህ ባርክ። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን አንተው ራስህ ተናግረሃል፤ በበረከትህም የባሪያህ ቤት ለዘላለም ይባረካል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በፊትህ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ የአገልጋይህን ቤት ለመባረክ ፈቃድህ ይሁን፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ በበረከትህ እንደ ተናገርክ የአገልጋይህ ቤት ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና አሁን እን​ግ​ዲህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በፊ​ትህ ይሆን ዘንድ የባ​ሪ​ያ​ህን ቤት እባ​ክህ ባርክ፤ በበ​ረ​ከ​ት​ህም የባ​ሪ​ያህ ቤት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይባ​ረክ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ተናግረሃልና አሁን እንግዲህ ለዘላለም በፊትህ ይሆን ዘንድ የባሪያህን ቤት፥ እባክህ፥ ባርክ፥ በበረከትህም የባሪያህ ቤት ለዘላለም ይባረክ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 7:29
6 Cross References  

ስለዚህ አሁን በፊትህ ለዘለዓለም እንዲኖር የባርያህን ቤት ለመባረክ ፈቅደሃል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አንተ የባረከው ለዘለዓለም ይባረካል።”


ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳያል፥ ይህንንም ለዘለዓለም ያደርጋል።”


ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቁጥጥሩም ሥር አደረጋቸው፥ ሜተግ አማ የተባለችውንም ከተማ ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ።


ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ሰውነታችሁ በሕይወት እንድትኖር ስሙኝ፥ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements