Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የጌታ ቁጣ ዖዛን ስለሰበረው ዳዊት አዘነ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፌሬጽ ዑዛ ተብሎ ይጠራል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የእግዚአብሔር ቍጣ ዖዛንን ስለ ሰበረው፣ ዳዊት ተከፋ፤ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፔሬዝ ዖዛ ተብሎ ይጠራል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የዚያ ስፍራ ስም “ፌሬጽዑዛ” እየተባለ ሲጠራ ይኖራል፤ እግዚአብሔር በቊጣ ተነሣሥቶ ዑዛን በመግደሉ ዳዊት እጅግ ተበሳጨ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ገደ​ለው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም “ዖዛ የሞ​ተ​በት” ተባለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ሰበረው ዳዊት አዘነ፥ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ተብሎ ተጠራ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 6:8
6 Cross References  

እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ።


ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ ክፉኛም አበሳጨው።


ዖዛ በድፍረት ይህን ስላደረገ፥ የጌታ ቁጣ በላዩ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀሠፈው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ።


ዳዊት በዚያን ቀን ጌታን ስለ ፈራ “የጌታ ታቦት እንዴት ወደ እኔ ይመጣል?” አለ።


ቀድሞም አልተሸከማችሁትምና፥ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነውምና ጌታ አምላካችን በመካከላችን ቊጣውን አወረደ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements