2 ሳሙኤል 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ይህ የአበኔር ንግግር እጅግ ያስቆጣው ኢያቡስቴ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት፥ ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ፥ ታማኝነቴን ሳላጎድል ይሄው አለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ ዛሬ ግን አንተ በዚህች ሴት ትከሰኛለህን? በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝ? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 አበኔርም በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ስለ ተቈጣ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለይሁዳ የምወግን የውሻ ጭንቅላት ነኝን? ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ ታማኝነቴን እስከ ዛሬ ድረስ አላጓደልሁም፤ አንተንም አሳልፌ ለዳዊት አልሰጠሁም፤ አሁን ግን አንተ ከዚህች ሴት ጋራ በፈጸምሁት ነገር ትከሰኛለህን? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የኢያቡስቴ ቃል አበኔርን በጣም አስቈጣው፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ ወደ ይሁዳ ነገድ የዞርኩ የማልጠቅም ውሻ ነኝን? እኔ ለአባትህ ቤት፥ ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነትን አሳይቼአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ ታዲያ፥ አንተ ስለዚህች ሴት ትወቅሰኛለህን? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አበኔርም ኢያቡስቴ እንዲህ ስላለው እጅግ ተቈጣ፤ አበኔርም እንዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም፥ ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኀጢአት ትከስሰኛለህ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አበኔርም በኢያቡስቴ ቃል እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፥ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኃጢአት ትከስሰኛለህ፥ በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? See the chapter |