Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 24:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዳዊትም ጋድን፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በጌታ እጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ታላቅ ስለ ሆነ በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅስ አልውደቅ” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ!” አለ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዳዊ​ትም ጋድን፥ “በሁ​ሉም እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ በሰው እጅ ከም​ወ​ድቅ ይልቅ ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዳዊትም ጋድን፦ እጅግ ተጨንቄአለሁ፥ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፥ በሰው እጅ ግን አልውደቅ አለው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 24:14
28 Cross References  

አቤቱ፥ ቸርነትህ እጅግ ብዙ ነው፥ እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


ዳዊትም ጋድን፦ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በጌታ እጅ ልውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለው።


ወደ ጌታ ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አስቀድሜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የፈለግሁትም ለዚህ ነበር፥ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉ የምትመለስ አምላክ እንደሆንህ አውቄ ነበርና።


ጌታ ለሁሉም ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው።


ይቅርታ በአንተ ዘንድ ነውና።


አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥


ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ ጌታም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፤ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።


በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ከእነርሱ ጋር ምሕረት አላደረግሽም፤ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፥ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


አቤቱ፥ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህና፥ ጽኑ ፍቅርህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።


በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ፥ ከቤት ሲወጣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማይቱን መክበባቸውን አየ፤ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ጠየቀው።


እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።


በእነዚህም በሁለቱ አማራጮች መካከል እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤


“አሁን ነፍሴ ታውካለች፤ ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ! ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።


እኔ ብዙም ሳልቆጣቸው እነርሱ ክፋትን ስላገዙት፥ በምቾት በሚኖሩት አሕዛብ ላይ እጅግ ተቈጥቻለሁ።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።


መፊቦሼት ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፥ “እንደ ሞተ ውሻ ለምቆጠር ለእኔ ይህን ያህል የምታደርግልኝ አገልጋይህ ኧረ ማን ነኝ?” አለ።


ከጌታ ጋር ጽኑ ፍቅር፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን አለና እስራኤል በጌታ ይታመን።


በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምትፈራቸውም ሰዎች እጅ ተላልፈህ አትሰጥም።


ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፥ ርኅራኄው አያልቅምና።


እንደገና ይራራልናል፤ በደሎቻችንን ይረጋግጣል፥ ኃጢአታቸውን ሁሉ በባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements