2 ሳሙኤል 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና ስሙም ከሦስቱ ኀያላን ጋር የሚጠራ ነበረ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ እርሱም ዝናን ያተረፈ ሰው ነበረ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 የጽሩያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ ዝነኞች የሆኑት የሠላሳዎቹ ወታደሮች አለቃ ነበር፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ ከሦስት መቶ ሰዎች ጋር በመዋጋት ሁሉንም ገደለ፤ ስለዚህም እንደ ሦስቱ ዝነኛ ሆነ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የሶርህያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበር። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ ስሙም በሦስቱ ዘንድ ተጠርቶ ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የጽሩያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሠላሳው አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ ስሙም እንደ ሦስቱ ተጠርቶ ነበር። See the chapter |