2 ሳሙኤል 21:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ በተደረገ ሌላ ጦርነትም፣ የቤተ ልሔሙ የዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን፣ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጋት ሰው የጎልያድን ወንድም ገደለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ቀጥሎም በጎብ ሌላ ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተደረገ፤ በዚህም ጊዜ የቤተልሔም ተወላጅ የሆነው የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውንና የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን ጎልያድ ተብሎ የሚጠራውን ሌላ ፍልስጥኤማዊ ገደለ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ደግሞም በሮም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ የቤተልሔማዊውም የዓሬኦርጌም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎዶልያን ገደለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፥ የቤተልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ። See the chapter |