Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ። በዚያን ጊዜም የሑሻው ተወላጅ ሲበካይ፥ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነውን ሳፍን ገደለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ሌላ ጦርነት ተደረገ። በዚያ ጊዜም ኩሳታዊው ሴቦካይ፣ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነውን፣ ሳፍን ገደለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ ጎብ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደረገ፤ በዚህን ጊዜ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ ሳፍ ተብሎ የሚጠራውን ከራፋይም ወገን የነበረውን ኀያል ሰው ገደለ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከዚ​ህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስ​ጣ​ጦ​ታ​ዊው ሴቤ​ኮይ ከራ​ፋ​ይም ወገን የሆ​ነ​ውን ሳፍን ገደ​ለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ሆነ፥ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሳፍን ገደለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 21:18
6 Cross References  

ኩሳታዊው ሴቤካይ፥ አሆሃዊው ዔላይ፥


እንደገና ጌት ላይ በተደረገው ጦርነት በእያንዳንዱ እጁና በእያንዳንዱ እግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም ዘር ነበረ።


ለስምንተኛው ወር ስምንተኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ኩሳታዊው ሲቦካይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ውስጥ ሀያ አራት ሺህ አባላት ነበሩ።


ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።


እነዚህ አራቱ በጌት የራፋይም ዘሮች የነበሩ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements