2 ሳሙኤል 20:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከዚያ አንዲት ብልኅ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፥ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብን ላነጋግርህ እንድችል ወደዚህ ና በሉት” አለቻቸው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 አንዲት ብልኅ ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ከከተማ ትጣራለች፤ “ስሙ! ስሙ! ለኢዮአብ የምነግረው ነገር ስላለ ወደዚህ እንዲመጣ ንገሩት” አለቻቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በከተማይቱ ውስጥ የምትኖር አንዲት ብልኅ ሴት በቅጽሩ ላይ ሆና ድምፅዋን ከፍ በማድረግ “ስሙ! ስሙ! ኢዮአብ ወደዚህ ይመጣ ዘንድ ንገሩት፤ እኔ ላነጋግረው እፈልጋለሁ!” አለች። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ከቅጥሩም አንዲት ብልሃተኛ ሴት፥ “ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮአብንም፦ እነግርህ ዘንድ ወደዚህ ቅረብ በሉት” ስትል ጮኸች። ወደ እርስዋም ቀረበ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ከከተማይቱም አንዲት ብልሃተኛ ሴት፦ ስሙ፥ ስሙ፥ ኢዮአብንም፦ እነግርህ ዘንድ ወደዚህ ቅረብ በሉት ስትል ጮኸች። See the chapter |