2 ሳሙኤል 19:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ስለዚህም ሕዝቡ በሙሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ተሻገረ። ንጉሡ ባርዚላይን ስሞ መረቀው፤ ባርዚላይም ወደ ቤቱ ተመለሰ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፣ ከመዓም ዐብሮት ሄደ። የይሁዳ ሰራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሰራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ንጉሥ ዳዊት በይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ታጅቦ ወንዙን ከተሻገረ በኋላ ወደ ጌልጌላ አቀና፤ ኪምሀምም አብሮት ተሻገረ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ንጉሡም ወደ ጌልገላ ተሻገረ፤ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ተሻገረ፤ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፥ ደግሞም የእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ከንጉሡ ጋር ተሻገሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ንጉሡም ወደ ጌልገላ ተሻገረ፥ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ደግሞም የእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ንጉሡን አሻገረው። See the chapter |