Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 19:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በላያችን ሆኖ እንዲገዛን የቀባነው አቤሴሎም ደግሞ በጦርነት ሞቷል፤ ታዲያ ስለ ንጉሡ የመመለስ ጉዳይ ለምንድን ነው ዝም የምትሉት?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የይሁዳ ሽማግሌዎችን እንዲህ በሏቸው አለ፤ ‘በመላው እስራኤል የሚባለው ሁሉ ለንጉሡ ባለበት የደረሰው ስለ ሆነ፣ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ንጉሥ ዳዊትም እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው የተናገሩትን ሰማ፤ ስለዚህም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን በመላክ የይሁዳን መሪዎች እንዲህ ብለው እንዲጠይቁአቸው አዘዘ፤ “ንጉሡን ረድታችሁ ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ ስለምን እናንተ የመጨረሻዎቹ ትሆናላችሁ?

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ንጉሡ ዳዊ​ትም ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ልኮ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለይ​ሁዳ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደር​ሶ​አ​ልና ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ንጉሡም ዳዊት ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ልኮ እንዲህ አላቸው፦ ለይሁዳ ሽማግሌዎች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩአቸው፦ የእስራኤል ሁሉ ነገር ወደ ንጉሡ ደርሶአልና ንጉሡን ወደ ቤቱ ከመመለስ ስለ ምን ዘገያችሁ?

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 19:11
11 Cross References  

ስለዚህ ሳዶቅና አብያታር የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መለሱት፥ በዚያም ተቀመጡ።


ይህም እኛን እንድትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ አድርገን ሰጠናችሁ እንጂ ሥልጣን ስላልነበረን አይደለም።


ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።


መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ እንግዲህ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።


ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያን የሠራዊቱ አዛዥ፥ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾመ።


በመላው የእስራኤል ነገዶችም፥ ሕዝቡ እንዲህ እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር፤ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ የታደገን እርሱ ነው፤ አሁን ግን በአቤሴሎም ምክንያት ከአገር ሸሽቶ ሄዶአል፤


ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፥ ኪምሃም አብሮት ሄደ። የይሁዳ ሠራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሠራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት።


ኢዮአብም፥ “ከእንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከአንተ ጋር ጊዜ ማጥፋት አልችልም” አለው፤ ስለዚህ በእጁ ሦስት ጦር ይዞ ሄደና አቤሴሎም እባሉጥ ዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ገና በሕይወት እያለ ወርውሮ በልቡ ላይ ተከላቸው።


እንዲሁም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ዐሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements