Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 18:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፥ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ ጌታ ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ እግዚአብሔር ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ቀጥሎም ኢትዮጵያዊው አገልጋይ እዚያ ደረሰና ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! የምሥራች ቃል ይዤልህ መጥቼአለሁ፤ በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡብህን ድል እንድታደርግ ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶሃል!” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እነ​ሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ይህ የተ​ነ​ሡ​ትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበ​ቀ​ለ​ልህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሡ ወሬ አም​ጥ​ቻ​ለሁ” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እነሆም፥ ኵሲ መጣ፥ ኵሲም፦ እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቼአለሁ አለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 18:31
11 Cross References  

ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ፥ “ጌታ ጠላቶቹን የተበቀለለት መሆኑን ሮጬ ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው” አለ።


ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።


አሒማዓጽም ጮኾ ንጉሡን፥ “ሁሉም ደህና ሆኖአል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፥ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ ጌታ አምላክህ የተመሰገነ ይሁን!” አለ።


አቤቱ፥ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፥ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኃይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፥ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።


ንጉሡም፥ “እልፍ በልና ቁም” አለው፤ ስለዚህ እልፍ ብሎ ቆመ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements