2 ሳሙኤል 18:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ሰዎቹ ግን፥ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት፥ ስለኛ ምንም አይገዳቸውም፤ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺህ ትበልጣለህ! ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ከቁም ነገር አይቈጥሩንም፤ ግማሾቻችን እንኳ ብንሞት ደንታቸው አይደለም፣ አንተ ግን ብቻህን ከእኛ ከዐሥሩ ሺሕ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ብትረዳን ይሻላል” አሉት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እነርሱም “አንተ ከእኛ ጋር መሄድ የለብህም፤ ጥቂቶቻችን ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ ወይም ግማሾቻችን ብንገደል ጠላት ምንም አይገደውም፤ አንተ ግን ከእኛ ዐሥሩን ሺህ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ አንተ እዚሁ በከተማይቱ ውስጥ ቈይተህ አስፈላጊውን ርዳታ ብትልክልን ይሻላል” አሉት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እነርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁላችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራዊት ስለሆንህ ብንሸሽ ልባቸው አይከተለንምና፥ እኩሌታችንም ብንሞት ልባቸው አይከተለንምና አትውጣ፤ አሁንም መርዳትን ትረዳን ዘንድ በከተማ ብትኖርልን ይሻለናል” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሕዝቡ ግን፦ አትወጣም፥ ብንሸሽ ስለ እኛ አያስቡም፥ ከእኛም እኩሌታው ቢሞት ስለ እኛ አያስቡም፥ አንተ ግን ለብቻህ ከእኛ ከአሥሩ ሺህ ይልቅ ትበልጣለህ፥ አሁንም በከተማ ተቀምጠህ ብትረዳን ይሻላል አሉ። See the chapter |