Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አቤሴሎም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የተባለች አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፤ ሴት ልጁም በጣም ውብ ነበረች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አቤሴሎም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የተባለች አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፤ ሴት ልጁም በጣም ውብ ነበረች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አቤሴሎም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ነበሩት፤ የሴት ልጁም ስም ትዕማር ሲሆን እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ለአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችና አን​ዲት ሴት ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የሴ​ቲቱ ልጅም ስም ትዕ​ማር ይባ​ላል። ያች​ውም ሴት መልከ መል​ካም ነበ​ረች፤ እር​ሷም የሰ​ሎ​ሞን ልጅ የሮ​ብ​አም ሚስት ሆና አቢ​ያን ወለ​ደ​ች​ለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ለአቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፥ የሴቲቱም ልጅ ስም ትዕማር ነበረ፥ እርስዋም የተዋበች ሴት ነበረች።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:27
6 Cross References  

አቤሴሎም፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፥ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል።


የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቆንጆ እኅት ነበረችው፤ የዳዊት ልጅ አምኖንም ወደዳት።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”


በእነርሱ ላይ እነሣለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፥ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል ጌታ።


አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements