Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ኢዮአብም መሬት ላይ በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡንም ባርኮ፥ ኢዮአብ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ልመና ስለተቀበልከኝ፥ አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን ዛሬ ለማወቅ ችያለሁ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኢዮአብም አክብሮቱን ለንጉሡ ለመግለጥ ወደ መሬት በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡንም ባረከ፣ ኢዮአብም በመቀጠል፣ “ንጉሡ የአገልጋዩን ልመና ስለ ተቀበለው፣ ባሪያህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቱን ዛሬ ለማወቅ ችሏል” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኢዮ​አ​ብም በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉ​ሡ​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን እን​ዳ​ገኘ አገ​ል​ጋ​ይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ኢዮአብም በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ እጅ ነሣ፥ ንጉሡንም ባረከ፥ ኢዮአብም፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የባሪያህን ነገር አድርገሃልና በዓይንህ ፊት ሞገስ እንዳገኘ ባሪያህ ዛሬ አወቀ አለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:22
13 Cross References  

ልጆችዋ ይነሣሉ፥ ምስጉን ነሽ ይሏታል፥ ባሏ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፦


ማን ነው ከአንጀቱ ያልባረከኝ፥ በበጎቼም ጠጉር ያልሞቀ?


የሰማችኝ ጆሮ ታሞግሰኝ፥ ያየችኝም ዐይን ትመሰክርልኝ ነበር፥


ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በፈቃደኝነት ራሳቸውን የሰጡትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።


ንጉሡም፥ “ኪምሃም ከእኔ ጋር ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማናቸውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።


ዳዊት ግን፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ በሚገባ ያውቃል፤ እርሱም በልቡ፤ ‘ዮናታን እንዳያዝን ይህን ማወቅ የለበትም’ ብሏል፤ ነገር ግን ሕያው ጌታን! በነፍስህ እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ቀርቷል” ብሎ ማለ።


ሞአባዊቱም ሩት ናዖሚንን፦ “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው ተከትዬ እህል ለመቃረም ወደ እርሻ ልሂድ” አለቻት። እርሷም፦ “ልጄ ሆይ፥ ሂጂ” አለቻት።


ይሁን እንጂ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ።


ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው፥ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው።


ንጉሡም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ፈቅጃለሁ፤ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው።


ከዚያም ኢዮአብ ወደ ገሹር ሄዶ አቤሴሎምን ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው።


የተቆዓዪቱም ሴት ወደ ንጉሡ ገብታ፥ በንጉሡ ፊት በግምባሯ በምድር ላይ ተደፍታ እጅ በመንሣት፥ “ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ” አለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements