Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ሄደ፤ እዚያ እንደደረሰም ከኢዮአብ የተቀበለውን መልእክት በሙሉ ለዳዊት ነገረው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ሄደ፤ እዚያ እንደ ደረሰም፣ ከኢዮአብ የተቀበለውን መልእክት በሙሉ ለዳዊት ነገረው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስለዚህም መልእክተኛው ወደ ዳዊት ሄዶ ኢዮአብ ያዘዘውን ሁሉ እንዲህ ሲል ነገረው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የኢ​ዮ​አ​ብም መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደር​ሶም ኢዮ​አብ የነ​ገ​ረ​ውን የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። ዳዊ​ትም በኢ​ዮ​አብ ላይ ተቈጣ። ያንም መል​እ​ክ​ተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተ​ማዋ ቅጥር ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? በቅ​ጥ​ሩም እን​ደ​ም​ት​ቈ​ስሉ አታ​ው​ቁ​ምን? የይ​ሩ​በ​ዓል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት በቴ​ቤስ የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ ቀረ​ባ​ችሁ?” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 መልእክተኛውም ተነሥቶ ሄደ፥ ኢዮአብም ያዘዘውን ሁሉ ለዳዊት ነገረው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 11:22
2 Cross References  

የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤጽ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ አንተም መልሰህ፥ ‘አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”


መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ አየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳደን መለስናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements