Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን አገልጋዮች ይዞ፥ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፥ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ፣ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፣ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቍረጥ መልሶ ሰደዳቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ በአንድ በኩል ጺማቸውን ላጨ፤ ልብሳቸውንም በመቊረጥ እስከ ወገባቸው አሳጥሮ አባረራቸው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሐኖ​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ገሚስ ላጨ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ከሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ሐኖንም የዳዊትን ባሪያዎች ወስዶ የጢማቸውን ገሚስ ላጨ፥ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 10:4
8 Cross References  

እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጉስቁልና ይነዳቸዋል።


ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ተልትለው፥ በጌታ ቤት ለማቅረብ የእህል ቁርባንና ዕጣን በእጃቸው ይዘው፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።


ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።


የራስ ጠጉራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቁረጡት።


ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፥ ሰዎቹ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር መልክተኞቹን ላከባቸው፤ ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪ፥ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements