Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚህም በኋላ ኢዩ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ገሠገሠ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮራም ገና ከቁስሉ አልዳነም ነበር፤ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ሊጠይቀው መጥቶ በዚያ ይገኝ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም ኢዩ በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ገሠገሠ፤ ይህን ያደረገውም ኢዮራም በዚያ ስለ ተኛና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም እርሱን ለመጠየቅ ወደዚያው ስለ ወረደ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም በኋላ ኢዩ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ገሠገሠ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮራም ገና ከቊስሉ አልዳነም ነበር፤ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ሊጠይቀው መጥቶ በዚያ ይገኝ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ አረ​ማ​ው​ያን የሶ​ርያ ሰዎች በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይታ​ከም ስለ ነበረ ኢዩ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ። ጠን​ካ​ራና ኀይ​ለኛ ሰው ነበ​ርና፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ራ​ምን ለማ​የት ወርዶ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኢዮራምም በዚያ ታምሞ ተኝቶ ነበርና ኢዩ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ። የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ኢዮራምን ለማየት ወርዶ ነበር።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 9:16
4 Cross References  

ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥


በኢይዝራኤል ከተማ መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ቃፊር ኢዩና ተከታዩ ጭፍራ ሲመጡ መቃረባቸውን አይቶ፥ “ሰዎች እየጋለቡ ሲመጡ አያለሁ!” ሲል የጥሪ ድምፅ አሰማ። ኢዮራምም “አንድ ፈረሰኛ ልከህ የሚመጡትን ሰዎች ሰላም ነውን? ብሎ እንዲጠይቅ አድርግ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements