2 ነገሥት 6:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 እርሱም፣ “አትግደላቸው፤ ለመሆኑ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸውን ትገድላቸው ዘንድ ይገባሃልን? አሁንም የሚበሉትንና የሚጠጡትን አስቀርብላቸው፤ በልተው ጠጥተውም ወደ ጌታቸውም ይሂዱ” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እርሱም፥ “በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸውን ግደል እንጂ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸው አይደሉምና አትግደላቸው። ይልቁንስ እንጀራና ውኃ በፊታቸው አቅርብላቸው፤ በልተውና ጠጥተውም ወደ ጌታቸው ይመለሱ” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 እርሱም “አትግደላቸው፤ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኸውን ትገድል ዘንድ ይገባሃልን? እንጀራና ውሃ በፊታቸው አኑርላቸው፤ በልተውና ጠጥተውም ወደ ጌታቸው ይሂዱ፤” አለው። See the chapter |