2 ነገሥት 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እርሷም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እርሷም ሄዳ ይህንኑ ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው። እርሱም፣ “ሄደሽ ዘይቱን በመሸጥ ዕዳሽን ክፈይ፤ የተረፈውም ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ ይሁን” አላት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም “እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን በሙሉ ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል” አላት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም፥ “ሄደሽ ዘይቱን ሽጭ ዕዳሽንም ክፈዪ፤ በተረፈውም ዘይት የአንቺንና የልጆችሽን ሰውነት አድኚ” አላት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም “ሄደሽ ዘይቱን ሽጪ፤ ለባለዕዳውም ክፈይ፤ አንቺና ልጆችሽም ከተረፈው ተመገቡ፤” አለ። See the chapter |