2 ነገሥት 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም “የሞዓብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” የሚል መልእክት ላከ። ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “አዎ እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ አንተ፥ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፥ ፈረሶቼን እንደ ፈረሶችህ መቁጠር ትችላለህ” ሲል ከመለሰ በኋላ፥ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮሣፍጥ፣ “የሞዓብ ንጉሥ ስለ ዐመፀብኝ ዐብረኸኝ ትዘምታለህን?” ሲል መልእክት ላከበት። እርሱም፣ “አዎን ዐብሬህ እዘምታለሁ፤ እኔ እንደ አንተው ነኝ፤ ሕዝቤ እንደ ሕዝብህ፤ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” በማለት መለሰለት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም “የሞአብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” የሚል መልእክት ላከ። ንጉሥ ኢዮሣፍጥም “አዎ እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ አንተ፥ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፥ ፈረሶቼን እንደ ፈረሶችህ መቊጠር ትችላለህ” ሲል ከመለሰ በኋላ፥ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥ፥ “የሞዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞዓብ ላይ ለሰልፍ ትሄዳለህን?” ብሎ፤ ላከ። እርሱም፥ “እወጣለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አንተም እንደ እኔ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥ “የሞዓብ ንጉሥ ዐምዖብኛልና ከእኔ ጋር በሞዓብ ላይ ለሰልፍ ትሄዳለህን?” ብሎ ላከ። እርሱም “እወጣለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው፤” አለ። See the chapter |