2 ነገሥት 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ሞዓባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፥ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው በመውጣት በጠረፉ ላይ ተጠባበቁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 በዚህ ጊዜ ነገሥታቱ ሊወጓቸው መምጣታቸውን ሞዓባውያን ሁሉ ሰምተው ነበርና፣ ልጅም ሆነ ሽማግሌ፣ መሣሪያ መያዝ የቻለ ሁሉ ተጠርቶ በመውጣት በጠረፉ ላይ ይጠባበቅ ጀመር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ሞአባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፥ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው በመውጣት በጠረፉ ላይ ተጠባበቁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ሞዓባውያንም ሁሉ እነዚያ ነገሥታት ሊወጉአቸው እንደ መጡ በሰሙ ጊዜ፥ “ሁላችሁ መሣሪያዎችን ይዛችሁ ርዱን” ብለው በሀገራቸው ሁሉ ጮኹ። ተሰበሰቡም፤ ወጥተውም በተራራው ራስ ላይ ቆሙ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ሞዓባውያንም ሁሉ ነገሥታት ሊወጉአቸው እንደ መጡ በሰሙ ጊዜ በወገባቸው ሰይፍ የሚታጠቁ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም በአገሩ ድንበር ላይ ቆሙ። See the chapter |