Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሔፍጺባ ተብላ የምትጠራ ነበረች፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ምናሴ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐምሳ ዐምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐፍሴባ ትባል ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሔፍጺባ ተብላ የምትጠራ ነበረች፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ምና​ሴም በነ​ገሠ ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ኀምሳ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም ሐፍ​ሴባ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ምናሴም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አምሳ አምስት ዓመት ነገሠ፤ የእናቱ ስም ሐፍሴባ ነበረ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 21:1
9 Cross References  

ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን ጌታ ደስታዬ ባንቺ ነው ብሏታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።


ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞፅን ወለደ፤ አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤


እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ።


ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ ታላቅ የቀብር ሥርዓት አደረጉለት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝቅያስ፥ ልጁ ምናሴ፥


ሕዝቅያስም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ።


ምናሴም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ኀምሳ አምስት ዓመት ነገሠ።


የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ፥ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


ሊያረክሱትም ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements