Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሀያ ዓመት ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ አምላኩን እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት ያደረገውን መልካም ነገር በእግዚአብሔር ፊት አላደረገም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ኻያ ዓመት ነበር፤ እርሱም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፤ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ አምላኩን እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አካዝ መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በታ​ማ​ኝ​ነት ቅን ነገ​ርን አላ​ደ​ረ​ገም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አላደረገም።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 16:2
14 Cross References  

አባቱም ዳዊት እንዳደረገ ሁሉ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ።


በፊተኛይቱ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና ጌታም ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበረ፤ በኣሊምንም አልፈለገም፥


ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተልና ለእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ታዛዥ በመሆን፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።


የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።


የአባቱንም የዖዝያን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፤


እርሱም የአባቱን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፤


አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።


አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በጌታ ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።


አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥


አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድና ለእኔም ብትታዘዝ፥ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።”


የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements