Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ በንጉሡ ዙሪያ ሁኑ፤ የሚቀርባችሁ ማንም ሰው ቢኖር ግን ይገደል። ንጉሡ በሚወጣበትም ሆነ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ዐብራችሁት ሁኑ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡ​ንም በዙ​ሪ​ያው ክበ​ቡት፤ የጦር ዕቃ​ች​ሁም በእ​ጃ​ችሁ ይሁን፤ በሰ​ል​ፋ​ች​ሁም መካ​ከል የሚ​ገባ ይገ​ደል፤ ንጉ​ሡም በወ​ጣና በገባ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ሁኑ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡንም በዙሪያው ክበቡት፤ የጦር ዕቃችሁም በእጃችሁ ይሁን፤ በሰልፋችሁ መካከል የሚገባ ይገደል፤ ንጉሡም በወጣና በገባ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሁኑ።”

See the chapter Copy




2 ነገሥት 11:8
7 Cross References  

ሌዋውያንም የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን በዙሪያው ይክበቡት፤ ወደ ቤቱም የሚገባ ይገደል ንጉሡም ሲገባና ሲወጣ ከእርሱ ጋር ሁኑ።”


ዮዳሄ በበኩሉ ዐታልያ በቤተ መቅደሱ ክልል ውስጥ እንድትገደል አልፈለገም፤ ስለዚህም የጦር አለቆቹን “ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርሷን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል” ሲል አዘዛቸው።


እርሱም የጌታ ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በእነርሱ ፊት የሚወጣ በእነርሱም ፊት የሚገባ እየመራቸውም የሚያስወጣቸው የሚያስገባቸው ሰው ይሁን።


ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው።


የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነ ጌታ በማኅበሩ ላይ አንድ ሰው ይሹም።


በሰንበት ቀን ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ግን በንጉሡ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements