Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 10:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ አሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ይኸውም ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን የገለዓድን ምድር ሁሉ ሲሆን፣ ይህም በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለው ከአሮዔር አንሥቶ የጋድን፣ የሮቤልንና የምናሴን አገር ገለዓድንና ባሳንን ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ሁሉ፥ በአ​ር​ኖን ወንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የጋ​ድ​ንና የሮ​ቤ​ልን የም​ና​ሴ​ንም ሀገር፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን መታ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን የገለዓድን አገር ሁሉ፥ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የጋድንና የሮቤልን የምናሴንም አገር፥ ገለዓድንና ባሳንን መታ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 10:33
9 Cross References  

በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።


አዛሄልም “ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን አሠቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ምርጥ የሆኑ ወጣቶቻቸውን ታርዳለህ፤ ሕፃናታቸውን በድንጋይ ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞች የሆኑ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትሰነጥቃለህ” ሲል መለሰለት።


ኢዩ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤


በዚያን ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በጋት ከተማ ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ወሰነ።


ከዚህም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ቤንሀዳድን ሦስት ጊዜ ድል ነሥቶ በአባቱ በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ቤንሀዳድ ይዞአቸው የነበሩትን ከተሞች አስመለሰ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements