2 ነገሥት 10:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ስለዚህም የበዓልን ነቢያት በሙሉ፥ በዓልን የሚያመልኩትንና ካህናቱን ጭምር በአንድነት ጠርታችሁ ሰብስቡልኝ፤ በምንም ምክንያት የሚቀር አይኑር፤ እኔ ለበዓል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ በዚያ የማይገኝ ማንም ሰው ቢኖር በሞት ይቀጣል።” ይህም ሁሉ በዓልን የሚያመልኩትን ሁሉ ለመግደል ኢዩ ያቀደው የተንኰል ዘዴ ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 አሁንም የበኣልን ነቢያት ሁሉ አገልጋዮቹንና ካህናቱንም በሙሉ ጥሩልኝ። ለበኣል ትልቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ አንድ ሰው እንኳ እንዳይቀር። የማይመጣ ሰው ቢኖር ግን በሕይወት አይኖርም” ኢዩ ግን ይህን ማድረጉ የበኣልን አገልጋዮች ለማጥፋት ተንኰል መፍጠሩ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ስለዚህም የባዓልን ነቢያት በሙሉ፥ ባዓልን የሚያመልኩትንና ካህናቱን ጭምር በአንድነት ጠርታችሁ ሰብስቡልኝ፤ በምንም ምክንያት የሚቀር አይኑር፤ እኔ ለባዓል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ በዚያ የማይገኝ ማንም ሰው ቢኖር በሞት ይቀጣል።” ይህም ሁሉ ባዓልን የሚያመልኩትን ሁሉ ለመግደል ኢዩ ያቀደው የተንኰል ዘዴ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 አሁንም የበዓልን ነቢያት ሁሉ፥ አገልጋዮቹንም ሁሉ፥ ካህናቱንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እንዳይቀር፤ ለበዓል ታላቅ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የቀረውም ሁሉ በሕይወት አይኖርም” አላቸው። ኢዩ ግን የበዓልን አገልጋዮች ያጠፋ ዘንድ በተንኮል ይህን አደረገ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 አሁንም የበኣልን ነቢያት ሁሉ፥ አገልጋዮቹንም ሁሉ፥ ካህናቱንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም አይቅር፤ ለበኣል ታላቅ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ የቀረውም ሁሉ በሕይወት አይኖርም፤” አላቸው። ኢዩም የበኣልን አገልጋዮች ያጠፋ ዘንድ በተንኰል ይህን አደረገ። See the chapter |