Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ቆሮንቶስ 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፥ ያን ያህል ማለታችን እንድታፍሩ ባይሆንም፥ እንዲህ በመመካታችን ግን እንድናፍር ያደርገናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋራ መጥተው ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም ያን ያህል በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ወደ እናንተ መጥተው ያልተዘጋጃችሁ ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን፤ እናንተማ በጣም ታፍራላችሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ምና​ል​ባት የመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመ​ጡና ሳታ​ዘ​ጋጁ ቢያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ እና​ንተ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ ባል​ልም እኛ ስለ እና​ንተ ከነ​ገ​ር​ና​ቸው የተ​ነሣ እና​ፍ​ራ​ለን።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡ፥ ያልተዘጋጃችሁም ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ፥ እናንተ እንድታፍሩ አላልንም እኛ ግን በዚህ እምነታችን እንድናፍር አይሁን።

See the chapter Copy




2 ቆሮንቶስ 9:4
7 Cross References  

እንደዚህ በመተማመን እየተመካሁ የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አይደለም።


በጎ ፈቃዳችሁን ስለማውቅ፤ በእናንተ ላይ የምመካበትን ምክንያት ለመቄዶንያ ሰዎች፥ “አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቶአል፤” ብዬ ተናግሬለሁ፤ ቅንዐታችሁም ብዙዎችን አነሣሥቶአል።


እንግዲህ ስለ ፍቅራችሁና ስለ እናንተ ያለን ትምክህት ማረጋገጫ እንዲሆነን በአብያተ ክርስቲያናት ፊት ይህን ለእነርሱ በግልጽ አሳዩ።


መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ለመርዳት ወደዋል።


እኔ በምመጣበት ጊዜ የገንዘብ መዋጮ እንዳይደረግ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ፤


እኔ ጳውሎስ “እኔ እመልሰዋለሁ፤” ብዬ በእጄ እጽፋለሁ፤ ከዚህም በላይ ለእኔ የራስህ ደግሞ ብድር እንዳለብህ አላስታውስህም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements